በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን በአንጋጫ ወረዳ በዞቤቾ ቀበሌ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
የከምባታ ዞን የኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሃንድኖ ለኢቢሲ ዶትስትሪም እንደገለፁት በዛሬው ዕለት ከሌሊቱ 11 ሰዓት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
በአደጋው የሁለት ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ሁለት ቤቶች ደግሞ በአደጋው ውድመት እንደደረሰባቸው ኃላፊው ገልፀዋል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች መልሶ ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ለመሰል አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብለው በተለዩ ስፍራዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች ተመሳሳይ አደጋ እንዳይደርስባቸው የቅድም ጥንቃቄ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
በላሉ ኢታላ
#ebc #ebcdotstream #landslide