ቴህራን በኒውክሌር መርሐ ግብሯ ዙሪያ ከዋሽንግተን ጋር የምታደርገውን ድርድር ለመቀጠል መዘጋጀቷን የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ተናገሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሜሪካ እና እስራኤል ሀገሪቱን ዳግም እንደማያጠቁ ስምምነት ላይ እስከተደረሰ ድረስ ሀገራቸው ድርድር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን ከአሻርክ አል አውሳት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
አክለውም አሜሪካ በፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን በሚገኙ የኒውክሌር ማብላያዎቿ ላይ ያደረሰችው ጥቃት የኢራንን አቋም አልቀየረም፤ ሀገሪቱ አሁንም ዩራኒየም የማበልፀግ መብቷን ማስጠበቅዋን ቀጥላለችም ነው ያሉት።
ከዚህ ቀደም የተደረገው ድርድር የተካረረ ነበር ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፥ “ድርድሩ ሳይጠናቀቅ እስራኤል እና አሜሪካ በኛ ላይ ጥቃት ሰንስዝረዋል በመሆኑም አዲስ ድርድር ቢካሄድ በእርግጠኝነት እንደቀደመው በዚህ መንገድ አይሆንም” ሲሉ ገልጸዋል።
በሰለሞን ከበደ