Search

የምስራቅና ደቡባዊ የአፍሪካ ሀገራት ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚረዳው ጉባዔ በአዲስ አበባ

ረቡዕ ነሐሴ 21, 2017 87

የምስራቅና ደቡባዊ የአፍሪካ ሀገራት  በወንጀል  ድርጊት የተገኘን ገንዘብ  ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀልን  መከላከል  ዓለማ ያደረገ ጉባዔ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀመሯል።

ጉባኤው በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣በሙስና ፣በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር በዕፆች ዝውውር የተገኘን ገንዘብ ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት፣ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ስርጭት ጨምሮ ሌሎች አመንጪ ወንጀሎችን በቅንጅት ለመከላከል አጋርነትን ማጠናከር ያለመ ነው።

በስብሰባው ላይ ከፖሊሲ አውጪዎች፣ ከፋይናንስ ደህንነት ተቋማት፣ ከህግ አስከባሪ አካላት፣ ከግሉ የፋይናንስ ዘርፍ ተቋማት እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ተቋማት የልዑካን ቡድኖችና ተወካዮች የተውጣቱ 1150 በላይ ተወካዮች ይሳተፉበታል።

.. 1999 በታንዛኒያ የተመሰረተው ቀጠናዊ ተቋም 21 አባል ሀገራት በተውጣጡ የፋይናንስ ደኅንነት ተቋማት፣ 1 ታዛቢ ሀገር እና የዓለም ባንክን፣ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትን ጨምሮ 34 አጋር ተቋማትንና ሀገራትን ያቀፈ ነው።

በላሉ ኢታላ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: