ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀልን ለመከላከል በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ ተናገሩ።
የምስራቅና ደቡባዊ የአፍሪካ ሀገራት በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀልን መከላከል ዓለማ ያደረገ 50ኛው የከፍተኛ ባለሙያዎች ግብረ-ኃይል ስብሰባ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።
ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ቀናት በሚካሄዱ መድረኮች ንቁ ሳታፊ በመሆን፤ ተሞክሮዋን ታካፍላለች ከሌሎችም ልምዶችን በመማር ድርሻዋን ትወጣለች ብለዋል።
ከፍተኛ ባለሙያዎች የሚያደርጓቸው ውይይቶችና ግምገማዎች አህጉሪቱ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝወውርን ለመቆጣጠር እንዲሁም ወንጀሎችን ለመከላከል እና ለውሳኔ ሰጪ አካላት ትልቅ ግብዓት እንደሚገኝበትም ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀልን ለመከላከል የሕግ ማሻሻያ ማድረግን ጨምሮ በርካታ ሥራዎችን እየሰራች እንደምትገኝም በመክፈቻው ተገልጿል።
በላሉ ኢታላ