የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 27ኛው የትምህርት ጉባዔ "የትምህርት ፍትሐዊነት እና ጥራት ለትውልድ ግንባታ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት፥ የተማረ የሰው ኃይል ለማፍራት እና የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ለውጦች ዘርፉን እያገዙ መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ በሰላም እጦት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችን መክፈትን ጨምሮ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፉን ስብራት ለመጠገን የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ምቹ የትምህርት ቤት ካባቢን መፍጠር፣ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን ማጠናከር እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የትምህርት ቁሳቁስን ማሟላት በበጀት ዓመቱ በትኩረት የሚፈፀሙ ተግባራት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ዲሳሳ፥ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ የትምህርት ዘርፍ የተጀመሩ ጥረቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በክልሉ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም በ74 ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ እንደሚገኝም ኃላፊው ገልፀዋል።
በነስረዲን ሀሚድ
#EBCdotstream #Education #Quality #Equity