Search

የፓስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ ለማንም ተቋም ሕጋዊ ውክልና አልሰጠሁም - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት

ረቡዕ ነሐሴ 21, 2017 271

ዜጎች አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ ለማደስም ሆነ የጠፋባቸውን ለመቀየር ቀጠሮ ሲያስይዙ በኦንላይን ራሳቸው መመዝገብ እንዳለባቸው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግረዋል፡፡

የፓስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ ለማንም ተቋም ሕጋዊ ውክልና አልተሰጠም ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ዜጎች አገልግሎት እንስፈጽማለን ወደየሚሉ አካላት ሄደው ተጨማሪ ወጪ ከሚያወጡ እና ከሚንገላቱ በግላቸው በኦንላይን እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ዜጐች ፓስፖርት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት ደግሞ ለ4 ሚሊዮን ዜጎች ፓስፖርት ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል አቶ ቢቂላ፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ የውጭ ዜጎች፣ ከዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ተሳታፊዎች ፣ ከቱሪዝም እና ከፓስፖርት አገልግሎት ከ34 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱንም ገልፀዋል፡፡  

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 12 ቅርንጫፎች የነበሩትን ሲሆን፤ የተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ አሁን ላይ የአገልግሎት መስጫውን ወደ 28 ማሳደጉንም ተቋሙ አሳውቋል።

ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት የነበረው ፓስፖርት በቅርቡ በኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት መቀየሩ አይዘነጋም።

 

በየተመኙሽ አያሌው