በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲካል ተሳፊ የሆኑ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ተወካዮች አለሎ-በድ ፍል ውሃን ጎብኝተዋል።
የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ተወካዮችም ከሰመራ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን አላሎ በድ ፍል ውሃ በማጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች በአሳይታ እና አፋምቦ የሚገኙ የቴምር እርሻዎችን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙ የአፋምቦ ሐይቅ እና ሌሎች የቱሪስት መስህቦችን እንደሚጎበኙም ተመላክቷል።

ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫሉ በክልሉ መካሄዱ አካባቢው ያለውን ተፈጥሮኣዊ ሃብት እና ባህሉን ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መሃመድ አሊ ለኢቲቪ ተናግረዋል።
በፌስቲቫሉ ለመሳተፍ ከተለያዩ ሀገራት ለመጡ ዜጎች ክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲያውቁ ተደርጓል ብለዋል።
የክልሉ ዋና ከተማ ሰመራ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫሉን ማዘጋጀቷ በቀጣይ ሌሎች መሰል መርሃ-ግብሮች እንዲታዘጋጅ ጥሩ ልምድ የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል።
በሁሴን መሀመድ