Search

እዳን ወደሃብት የቀየረው የአፍሪካውያን ኩራት - የሕዳሴ ግድብ

ረቡዕ ነሐሴ 21, 2017 251

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከፍጻሜው ደርሷል፤ የበርካቶችን የይቻላል መንፈስ ያጎለበተው የግድቡ ግንባታ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያንም ጭምር የልማት ተምሳሌት መሆኑን ምሁራን እየገለጹም ይገኛል።   

አምባሳደር ስለሺ በቀለ፤ ሕዳሴ አፍሪካ ከገነባቻቸው የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች ግዙፉ እና ወሳኝ ድርሻ ያለው መሆኑን በኢቢሲ በዛሬይቱ ኢትዮ”ጵያ ነገን ዛሬ በተሰኘ መሰናዶው ላይ አንስተዋል።

ግድብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ኩራት ነው ያሉት አምባሳደር ስለሺ፤ ለጎረቤት ሃገራትም ትልቅ የኢነርጂ አቅርቦትን የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል።  

የግድቡ ግንባታ አፍሪካውያን ሃብት አሰባስበው እራሳቸውን ማልማት እንደሚችል በተግባር የታየበትም ነው ብለዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (/) በበኩላቸው፤ ሕዳሴ ግድብ የመቻላችን ምክንያት፤ ሌላኛው የዐድዋ ድል ነው ሲሉ ገልፀውታል።

ግድቡ በኢትዮጵያውያን ላብ እን ደም የተገነባ የወል ታሪካችን፤ የጋራ ምልክታችንም ነው ብለዋል።   

ሕዳሴ በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ለምርቃቱ የተቃረበ መሆኑን አንስተው፤ ግድቡ የአፍሪካውያን ቀጣናዊ ትስስር የሚያጠናክር የፓን-አፍሪካን ፕሮጀክት መሆኑንም አስረድተዋል።

ሕዳሴ እዳን ወደሃብት የቀየረ ትልቅ ግድብ ነው ሲሉም ተስፋዬ በልጅጌ (/) ተናግረዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል እና የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተዳራዳሪ ቡድን አባል አምባሳደር ዘሪሁን አበበ በበኩላቸው፤ ሁሉንም የዘላቂ የልማት ግቦች እንድናሳካ ከሚያስችሉ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው ብለዋል።

ግድብ ዲፕሎማሲውና የተግባር ሥራችን እየተደጋገፈ እንደሀገር ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ደርሰናል ሲሉም ገልጸዋል።