ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን ማስተናገዷን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) ገለፁ።
በፊት በጣት ከሚቆጠሩ ሁነቶች በላይ ማዘጋጀት ከባድ ነበር ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፥ አሁን ላይ እነዚህን መንግሥት የሰራቸዉ ትላልቅ የመሰረተ ልማቶች ለኮንፈረንስ ቱሪዝሙ ማደግ አስተዋፅኦ እንዳደረጉ ገልጸዋል።
በተለይም በአዲስ አበባ የመሰረተ ልማት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች መሟላት ከተማዋን ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ተመራጭ እንዳደረጋት አንስተዋል።
መንግሥት ኮንፈረንስ ቱሪዝምን ለማሳደግ ትኩረት በመስጠቱ እንዲሁም የሀገሪቱ የዲፕሎማሲ አቅም እየጎለበተ መምጣት በዘርዱ ከፍተኛ ለዉጥ ማምጣቱን ገልጸዋል።
ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ማደግ የተሰሩ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን ማስፋት እና መሠረተ ልማቶችን መገንባት ሚናዉ ከፍተኛ እንደነበርም ጠቁመዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ