በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በጫራቃ እና በሀሮ ቀበሌ ትላንት ከምሽቱ 5 ሰዓት አከባቢ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በደረሰ የመሬት ናዳ እስካሁን የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የጌዴኦ ዞን ፖሊስ ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር ብሩ ማርቆስ ለኢቢሲ እንደገለጹት፤ ትላንት ማምሻውን በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ ለአደጋው ምክንያት ሆኗል።
በመሬት ናዳው ከሞቱ 9 ሰዎች መካከል 6 ወንዶች ሲሆኑ የተቀሩት ሴቶች መሆናቸውንም አመላክተዋል።
አካባቢው ለናዳ አደጋ ተጋላጭ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባልም ተብሏል።
በተመስገን ተስፋዬ