የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር የተደረገውን የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ስምምነት የኢትዮጵያ የማያቋርጥ የአድገት ጉዞ የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑ ገለፁ።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ በዓመት እስከ 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ለማምረት የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።
ዳንጎቴ በአፍሪካ ትልቅ የማዳበሪያ ፋብሪካ ያለዉ ሲሆን ላለፉት 15 ዓመታት የሲሚንቶ ፋብሪካ ገንብቶ ስራ ላይ ያለ ተቋም ነዉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና ዳንጎቴ ግሩፕ የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ማድረጋቸውንም አንስተዋል።
ለግብርና ግብአት የሚሆን ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የ40 በመቶ ድርሻ ሲኖረዉ ዳንጎቴ 60 በመቶ ድርሻ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም ወደ ስራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ግንባታው በአርባ ወራት ለማጠናቀቅ መታቀዱን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው፤ በመንግሥት በሚደረግለት ድጋፍ ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ሁሉም ብትብብር እንደሚሰራም ተናግረዋል።
ፋብሪካው በሶማሊ ክልል ጎዴ እንደሚሰራ እና በአጠቃላይ በሀገር ደረጃ የፔትሮ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ማቋቋም እንዲቻል ተሳቢ መደረጉን ገልጸዋል።
በቢታንያ ሲሳይ
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #DangoteGroup #Fertilizer