Search

የሩስያና ሰሜን ኮሪያ መሪዎች በቤጂንግ በሚካሄደው ግዙፍ ወታደራዊ ትርዒት ላይ ይገኛሉ

ሓሙስ ነሐሴ 22, 2017 81

በቅርቡ በቻይና ቤጂንግ ቲያናንመን አደባባይ በሚካሄደው ወታደራዊ ትርዒት ላይ የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እንደሚገኙ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጠናቀቀበትን 80ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በቻይናዋ ርእሰ መዲና ቤይጂንግ በቀጣይ ሳምንት በሚደረገው ግዙፍ ወታደራዊ ትርዒት ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮች ቻይና የደረሰችበትን ወታደራዊ ቴክኖሎጂ በሚያሳዩ የተለያዩ ዘመናዊ አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችና ተዋጊ አውሮፕላኖች ትርዒት እንደሚያሳዩ ተገልጿል።

በዚህ ዝግጅት ላይ የሩስያና ሰሜን ኮሪያ መሪዎች፣ የኢራን ፕሬዚዳንት መስኡድ ፔዜሽኪያን እንዲሁም የቤላሩስ እና የኪውባ መሪዎችን ጨምሮ የ26 ሀገራት መሪዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

በዋሲሁን ተስፋዬ

#China #Beijing #TiananmenSquare #militaryparade #XiJinping #KimJongUn #VladimirPutin