በሩሲያ እና በቻይና መካከል ባለፉት ሦስት ዓመታት ያለው ንግድ በ67 በመቶ ማደጉን በቻይና የሩሲያ አምባሳደር ኢጎር ሞርጉሎቭ ለስፑትኒክ አሳውቀዋል።
የቻይና የጉምሩክ አጠቃላይ አስተዳደር መረጃም ፤ እ.አ.አ. በ2024 የሁለትዮሽ ንግዱ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ1.9 በመቶ አድጎ፣ 244.8 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ አዲስ ክብረ ወሰን ማስመዝገቡን ገልጿል።
አምባሳደር ኢጎር ሞርጉሎቭ፤ በርካታ የምዕራባውያን ኩባንያዎች ከሩሲያ ገበያ ሲወጡ፣ በፍጥነት የተተኩት የቻይና የንግድ ተቋማት አስፈላጊ የሆኑ ሸቀጦችን በበቂ መጠን እያቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል።