መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ወደ ክልሎች የማስፋፋት ሥራ በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዳምጠው ገመቹ ገለፁ።
በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ፣ በሻሸመኔ ፣ በቢሾፍቱ እና በሸገር ከተማ አስተዳደሮች ላይ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በቀጣይ ዓመት መጀመሪያ ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።
አገልግሎቱ ከወረቀት ነፃ በሆነ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንደሚሆን ጠቁመው፤ ከአሁን በፊት የነበሩ ብልሹ አሰራሮችን ያስቀራል ሲሉ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ጉዳይ ለማስፈፀም ተብሎ የሚጠየቁ የዕጅ መንሻዎችን ለማስቀረት አስተዋፅኦ እንዳለዉ አንስተዋል።
በሁለተኛው ምዕራፍ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን በዋና ዋና ከተሞች ፣ በዞን አስተዳደር ከተሞች እንዲሁም በታችኛው የአስተዳደር ደረጃዎች ላይ ለመተግበር ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል ።
በቢታኒያ ሲሳይ