Search

ኢትዮጵያ የዓባይ ውሀ የሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ሀብት ነው ብላ ታምናለች

ዓርብ ነሐሴ 23, 2017 29

ኢትዮጵያ የዓባይ ውሀ የሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ሀብት ነው ብላ እንደምታምን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (/ /) ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን የገነባችበት መንገድ ፍትሐዊ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡

በግድቡ የግንባታ ሂደት በተለይም በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ይነሱ የነበሩ ጉዳዮች ከእውነት ያፈነገጡ ፕሮፓጋንዳዎች ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ በግድቡ የውሀ አጠቃቀም ላይም ሆነ ሌሎች የደህንነት ስጋቶች የሌሉበት መሆኑን በአለም አቀፍ ሙያተኞች የተሰነደ መረጃን በማቅረብ ማረጋገጧን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው አንስቶ የዓባይ ወንዝ የሁሉም አፍሪካውያን ጥቅም ስለመሆኑ ደጋግማ ገልጻለችም ብለዋል፡፡

የህዳሴው ግድብ ተደራዳሪ እና የውሀ ምህንድስና ባለሙያ በለጠ ብርሀኑ (/) በበኩላቸው፤ የህዳሴው ግድብ የኃይል ማመንጫ በመሆኑ የውሀውን ፍሰት እንደማያግድና ይልቁንም የተረጋጋ የውሀ ፍሰት እንዲኖር እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

የውሀ ሙሌቱ ሂደት የሚከናወነው ውሀ በሚበዛበት የክረምት ወቅት በመሆኑ የተፋሰስ ሀገራትን ከጎርፍ እና ከአላስፈላጊ አደጋዎች እንደሚከላከልም አስገንዝበዋል፡፡

የውሀ ፍሰት ልኬቱ ሁሉንም ተጠቃሚ ያደረገ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

የተሻጋሪ ውሀ አካላት የተለያዩ መሰረታዊ ህጎች እንዳሉት የተናገሩት የምህንድስና ባለሙያው፤ ፍትሀዊነት፤ ምክያንያታዊ ተጠቃሚነት እና የከፋ ጉዳት አለማድረስ ዋነኞቹ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በዚህ ረገድ የህዳሴው ግድብ እነዚህን ህጎች መሰረት አድርጎና አክብሮ መከናወኑን ገልፀዋል፡፡

በሜሮን ንብረት

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #GERD