Search

የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል ወታደሮችን እያስመረቀ ነው

ቅዳሜ ነሐሴ 24, 2017 178

በመከላከያ ሚኒስቴር በሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ10ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እያስመረቀ ይገኛል።

ምልምል ወታደሮቹ መሰረታዊ የወታደራዊ ሳይንስ፣ የፅንሰ ሀሳብና የተግባር ስልጠና መውሰዳቸው የተገለፀ ሲሆን፤ የሚሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት መፈፀም የሚችሉ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመከላከያ ሚኒስቴር የሰው ሀብት ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል ሀጫሉ ሸለመ፣ የመከላከያ ሰላም ማስከበር ኃላፊ ሜጀር ጄነራል አዳምነህ መንግሥቴ፣ የሠራዊቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ መኮንኖችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

በቴዎድሮስ ታደሰ

#EBCdotstream #Hurso #graduation #soldiers