በአማራ ክልል የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ፈትተዋል።
በርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ደርቤ መኩርያው እና የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ጄኔራል ዋኘው አለሜን እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የሰላም አማራጩን የተቀበሉ ታጣቂዎች ለተሃድሶ ስልጠና ጠዳ ጊዜያዊ ማሰልጠኛ መግባታቸውን ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#EBCdotstream #AmharaRegion #Disarmament