Search

ሉሲ እና ሰላም በፕራግ መታየታቸው ቱሪዝሙን ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ ፈጥሯል - የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን

ቅዳሜ ነሐሴ 24, 2017 55

የድንቅ ነሽ (ሉሲ) እና የሰላም ቅሪተ አካላት በቼክ ሪፐብሊክ ፕራግ ከተማ መጎብኘታቸው ኢትዮጵያን በአውሮፓ አህጉር ለማስተዋወቅ አይነተኛ ሚና እንዳለው የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ቅሪተ አካላቱ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን በተገቢው መንገድ ማስተዋወቅ ያስቻሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

 በከተማው ዋና ዋና ሙዚየሞች ቅርሶቹ እየተጎበኙ መሆኑን አመላክተው፤ በኤግዚቢሽኑ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ስለመሆኑም አስረድተዋል።

ፕራግ ከተለያዩ አውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ ቱሪስቶች የሚጎበኞት ታሪካዊ ከተማ በመሆኗ ኢትዮጵያን ይበልጥ ለማስተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

 

በሜሮን ንብረት

 #Ebc#Ebcdot stream #Lucy and selam #Ethiopia tourism #