የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከነሀሴ 25 እስከ 26 በሚካሄደው የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ቻይና ቲያንጂን ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቲያንጂን በክብር ዘብ እና በቀይ ምንጣፍ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ፑቲን በአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝታቸው የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፤ በቻይና ወታደራዊ ትርዒት ላይ እንደሚታደሙም ተነግሯል፡፡
የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ በዋናነት በቀጠናዊ የጸጥታ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር መሆኑ ተገልጿል፡፡
በጉባኤው ላይ 20 በላይ የሀገራት መሪዎች፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡
ቭላድሚር ፑቲን በቻይና ቆይታቸውም ፕሬዚዳን ሺ ጂንፒንግን፣ የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ጨምሮ የተለያዩ መሪዎችን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከጉባኤው መጠናቀቅ በኋላ የሚከናወነው የቻይና ወታደራዊ ትርዒት ላይ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡንን ጨምሮ የ26 ሀገራት መሪዎች እንደሚታደሙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
#ebc #ebcdotstream #VladimirPutin #china #SCO