Search

የተጨነቀን ሰዉ ከረዳሁ እፎይ ብዬ እዉላለሁ - የከዚራዋ እናት

እሑድ ነሐሴ 25, 2017 56

ወይዘሮ ከበቡሽ ቡርኖ ይባላሉ፤ ከአስር አመት በላይ በህክምና ሞያ አገልግለዋል።

ወይዘሮ ከበቡሽ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ በሚሠሩት ሥራ በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ የተወደዱና የተከበሩ ናቸው።

ሰውን ማገዝ ማለት ሁልጊዜ ህሊናን ማፅዳት ማለት ነው የሚሉት / ከበቡሽ፤ ለተቸገሩ ቤታቸውን ለቀው የሚያሳድሩ የደግነት ምሳሌ ናቸው።

የድሬደዋ ከተማ የመንደር አድባር የሆኑት / ከበቡሽ በህክምና ሞያ ለማህበረሰቡ እርዳታ በማድረግ ይታወቃሉ፡፡

የከተማው ቀበሌ ሊቀመንበር በነበሩባቸው ጊዜያትም ለብዙዎች እርዳታን ያደርጉ እንደነበር ጓደኞቻቸው ይመሰክራሉ።

ከቀበሌ ሊቀመንበርነት የጀመረው ሰው የመርዳት ጉዟቸው፤ ሆስፒታል ዉስጥ 10 ዓመት ሰዎችን በማገዝና ምክር በመስጠት የበርካቶችን ሕይወት እንዲቀይሩ አስችሏቸዋል።

የአምስት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ ከበቡሽ፤ እናትና አባት የሌላቸውን ልጆች በማሳደግ ራሳቸውን እንዲችሉ አድርገዋል።

እሳቸው ጋር ቀርቦ የተጠማ፣ የተራበ እንዲሁም ቤት የሌለው ባጠቃላይ የተቸገረ መፍትሄ ያገኛል ሰብሳቢያችን ናቸው ይሏቸዋል የአካባቢው ሰዎች።

/ ከበቡሽ እሩህሩህ ለተቸገሩ የሚደርሱ የልጆቻቸውን ልብስ ሳይቀር አንስተው የሚያለብሱ ማደሪያ ላጡ ቤታቸውን ለቀው የሚያሳድሩ ደግ እናት ናቸው ሲሉም ይገልጿቸዋል።

በድሬደዋ ከተማ ጎዳናዎች ላይ ያሉ አቅመ ደካሞችን የሚጎበኙ ሲሆን ብዙ እናት አባት የሌላቸውን ህፃናት በማሳደግ ለቁም ነገር አብቅተዋል።

ታድያ ሁሉም ሰው ለኔ እኩል ነው ህሊናዬን የማስደስተው ሰው በመርዳት ነው ይላሉ።

በቢታንያ ሲሳይ እና ሔለን ተስፋዬ

#ebcdotstream #ebc #Ethiopia #diredewa