በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም ምርጫ በታላቅ ስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
ነሐሴ 25 ቀን 2017 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ፣ የ2017 የከተማውን መጅሊስ የማዋቀር ሂደትና የምርጫ መርሃ ግብር በሰላማዊና ኢስላማዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መንገድ በስኬት ማጠናቀቁን በታላቅ ደስታ ይገልፃል።
መንግሥት የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም፣ የፌደራል መጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ በወሰነው መሰረት “ምርጫ ለፅኑ ተቋም” በሚል መሪ ቃል ህዝብ መሪውን በመስጂዱ በነፃነት ሊመርጥ ችሏል።
ቦርዱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት አምስት ወራት ከ 5 ሺ በላይ የምርጫ ግብረ ሀይል አባላት በበጎ ፈቃደኝነት በማሳተፍ ፣ የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም እና የሀገራችንን ጥንታዊ የእስልምና ታሪክ የሚያንፀባርቅ ኢስላማዊ ስነ ስርዓቱን የጠበቀ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ሌት ተቀን ሲሰራ ቆይቷል።
ይህንንም የተቀደሰ ዓላማ ለማሳካት በየደረጃው ማለትም በክፍለ ከተማ፣ በወረዳ እና በመስጂድ ደረጃ የምርጫ አስፈጻሚዎችን በመሾም እና ግብረ ኃይሎችን በማደራጀት እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የመጅሊስ ስራ አስፈፃሚዎችን በማስመረጥ ሰፊ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።
የዚህ የተቀናጀ ጥረት ፍፃሜ የሆነው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምሥረታ ጉባኤ፣ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወከሉ የዑለማዎች፣ የምሁራን፣ የሰራተኛ ማህበረሰብ፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
የምርጫው ሂደት ኢስላማዊ ሂደቱን የጠበቀ ግልጽ፣ ሰላማዊ እና ሁሉንም ያሳተፈ ሆኖ በላቀ ስኬት ተጠናቋል።
በዚህም መሰረት የምርጫው ውጤት እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
1. አዲስ አበባን በፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሚወክሉ ተመራጮች
ከዑለማ ዘርፍ፡
1. ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ
2. ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
3. ሸይኽ ሑሴን በሽር
4. ሸይኽ ማሕመድ ሑሴን
5. ሸይኽ አሕመድ ዛኪር
ከምሁራን ዘርፍ፡
1. ኤልያስ አወል
2. አምባሳደር ሸሪፍ ኸይሬ
ከሰራተኛ ማኅበረሰብ ዘርፍ፡
1. አብድልቃድር ማሂ
ከወጣት ዘርፍ፡
1. ኢብራሂም ሙሰማ
ከሴቶች ዘርፍ፡
1. ዘይነብ ኑሩ
2. የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ተመራጮች
ከዑለማ ዘርፍ፡
1. ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ
2. ሸይኽ ሙሐመድ ሸሪፍ
3. ኡስታዝ ጋሊ አባቦር
4. ሸይኽ ዙበይር ሬድዋን
5. ሸይኽ ሑሴን ሰዒድ
6. ኡስታዝ ሰልሃዲን መለሰ
7. ሸይኽ ኑርሑሴን ሙስጠፋ
ከምሁራን ዘርፍ፡
1. ሺሃቡዲን ኑራ
2. ሼህ መሐመድ አሊ
ከማኅበረሰብ ዘርፍ፡
1. ኡስታዝ አዩብ ደርባቸው
ከወጣቶች ዘርፍ፡
1. መንሱር ኸድር
ከሴቶች ዘርፍ፡
1. ፈትህያ ሙሐመድ
2. ኑርያ ሙሐመድ
በኦዲትና ኢንስፔክሽን፡
1. ዶ/ር ዘይኑ ዙበይር
2. አቶ ሙሐመድ አብዶሽ
3. አቶ በረከት አብደላ
በተጨማሪም ጉባኤው የከፍተኛ ምክር ቤቱን ቁልፍ አመራሮች የሰየመ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት፡-
1. ሸይኽ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባ - የከፍተኛ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት፣
2. ሸይኽ ሙሐመድ ሸሪፍ - ምክትል ፕሬዝዳንት፣
3. ሺሃቡዲን ኑራ - ዋና ጸሐፊ ሆነው ተመርጠዋል።
በመጨረሻም ምርጫ አስፈጻሚ ቦርዱ ለተመረጡት አባላትና አመራሮች በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን እያስተላለፈ፣ በቀጣይ የኃላፊነት ዘመናቸው የከተማችንን ሙስሊም ማኅበረሰብ በላቀ ኃላፊነትና ቅንነት እንዲያገለግሉ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡
ለዚህ ታላቅ ስኬት የበኩላቸውን ላበረከቱት ለሰላም ሚንስቴር፣ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ለከተማዋ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስና በየደረጃው ለሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች እንዲሁም ለመላው የአዲስ አበባ ሙስሊም ነዋሪዎች በአላህ ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ጉ/ከ/ም/ቤት