በቦረና የተገነባው የያቤሎ ኤርፖርት ስራ መጀመሩ የአካባቢውን ባህል ከማስተዋወቅ ባለፈ ንግድ እና ቱሪዝም እንዲስፋፋ የሚያስችል ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የያቤሎ ኤርፖርትን መርቀው ሥራ ባስጀመሩበት መርሐ-ግብር ላይ ነው።
የገዳ ሥርዓትን ጠብቆ ያቆየው የቦረና ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ልዩ ሥፍራ ያለው መሆኑን በንግግራቸው ገልፀው፤ የአየር ማረፊያው ሥራ መጀመር ለኢንቨስትመንት በር ከፋች መሆኑን አክለዋል።
የገጠመውን ችግር አልፎ በዘላቂነት ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ ያለው የአካባቢው ማህበረሰብ ሀብቱ የሆነውን የአየር ማረፊያ በአግባቡ እንዲጠብቅ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በአፎሚያ ክበበው
#EBCdotstream #DPMTemesgen #Yabelo #Airport