ከመሃል ሀገር ርቀው ለሚገኙ አካባቢዎች መሠረተ ልማቶችን በማሟላት ያላቸው ትስስር እንዲጠናከር እየተሠራ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ።
የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጠው የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ ምረቃ እና ሥራ ጅማሮም የዚህ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
"ቃላችንን በተግባር እውን ማድረግ ችለናል" ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ወጣ ብለው የሚገኙ አካባቢዎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር እንዲኖራቸው እየተሠራ መሆኑን አክለዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው፥ በአራቱም የሀገሪቱ ጫፎች ያሉ ዜጎችን በአቪዬሽን ለማስተሳሰር እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
አየር መንገዱ የመሠረተ ልማት ግንባታ ማካሄድ እና አውሮፕላኖችን ማዘመንን ጨምሮ የተለያዩ ማሻሻያዎችን እያደረገ ስለመሆኑ አውስተዋል።
ለ80 ዓመታት የተሟላ የአየር ትራንስፖርት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አድማሱን እያሰፋ እንደሚቀጥል ያረጋገጡት ደግሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚው መስፍን ጣሰው ናቸው።
በአፎሚያ ክበበው
#EBCdotstream #ETV #Yabelo #Airport
#EBCdotstream #ETV #Yabelo #Airport