Search

አውሮፓ ልትጠፋ ትችላለች፡- ኢሎን መስክ

ሰኞ ነሐሴ 26, 2017 44

የቴክኖሎጂ ባለጋው ኢሎን መስክ፣ አውሮፓ የወሊድ ምጣኔን ካላሳደገች "ልትጠፋ" እንደምትችል አስጠንቅቀዋል።

የመስክ ማስጠንቀቂያ የተሰማው በስኮትላንድ የወጣውን መረጃ መሰረት በማድረግ ነው።

መረጃው እንደሚያሳየው፣ በ2025 የመጀመሪያ አጋማሽ በስኮትላንድ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተወለዱት በ34 በመቶ ይበልጣል።

መስክ የህዝብ ቁጥር ራሱን ለመተካት የሚያስፈልገው አማካይ የወሊድ ምጣኔ (replacement rate) 2.1 መሆን አለበት ብሎ ያምናል።

ሆኖም በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች ይህ ቁጥር በቂ ላይሆን እንደሚችል እና እስከ 2.7 ድረስ ሊደርስ እንደሚገባ ይጠቁማሉ።

የእንግሊዝ ስታቲስቲክስ ቢሮ እንደገለጸው፣ በ2024 በእንግሊዝ እና ዌልስ የወሊድ ምጣኔ 1.4 ሲሆን፣ በስኮትላንድ ደግሞ 1.3 ነው። ይህም ከሚፈለገው ምጣኔ በእጅጉ ያነሰ ነው።

መስክ የወሊድ ምጣኔ ማሽቆልቆል ከአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ ለሥልጣኔ አደጋ ነው ሲል በተደጋጋሚ አስጠንቅቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ የዓለም አማካይ የወሊድ ምጣኔ ከ50 ዓመታት በላይ ሲያሽቆሎቁል ቆይቷል። በ1970ዎቹ 5 የነበረው ምጣኔ፣ በ2024 ወደ 2.2 ወርዷል።

እ.ኤ.አ. በ2024 ከዓለም ሀገራት ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት ብቻ የወሊድ ምጣኔያቸው 2.1 እና ከዚያ በላይ ነበር። ከእነዚህ ሀገራት አብዛኛዎቹ የሚገኙት ከሰሃራ በታች ባለው የአፍሪካ ክፍል ሲሆን፤ ከእስያ የመን እና አፍጋኒስታን ይገኙባቸዋል።

ሩስያም ብትሆን የወሊድ ምጣኔ ማሽቆልቆል ችግር ውስጥ ገብታለች። በ2024 በሩስያ 1.2 ሚሊዮን ሕፃናት ብቻ የተወለዱ ሲሆን፤ ይህም ከ1999 ወዲህ ዝቅተኛው ቁጥር ነው። የወሊድ ምጣኔዋም 1.4 መድረሱን አር ቲ ዘግቧል።

በሰለሞን ገዳ

#demography #fertilityrate #replacemntrate #birthrate #deathrate