ከመሬት በታች በ8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተፈጠረ እንቅስቃሴ በምስራቅ አፍጋኒስታን የመሬት መንቀጥቀጥ አስከትሏል::
በምስራቃዊ አፍጋኒስታን በሬክተር ስኬል 6 ሆኖ የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ የብዙዎችን ህይወት ቀጥፏል::
ቢቢሲ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት አረጋገጥኩኝ ብሎ እንደዘገበው እስከአሁን ከ20 በላይ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል::
እንዲሁም ከመቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በተለያየ መጠን ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸውን ከባለስልጣናቱ አረጋግጧል::
ይሁን እንጂ በአንዳንድ ሚዲያዎች ከ2 መቶ በላይ ዜጎች ህይወታቸው እንዳለፈ እየዘገቡ ሲሆን ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ግን ማረጋገጫ የለውም::
አደጋው ከባድ በመሆኑ ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ግን ተገልጿል::
የነፍስ አድን ሰራተኞች በሄሊኮፕተር እና መኪና በመታገዝ ተጎጂዎችን ወደ ሕክምና በመውሰድ ላይ ናቸው::
አፍጋኒስታን ላለፉት ተከታታይ ሦስት ዓመታት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እያጋጠማት ቆይቷል::
በ2023 በምዕራብ አፍጋን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 6.3 ሆኖ የተመዘገበ እና ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን ያጡበት ነበር::