ቻይናዊው የ19 ዓመቱ ሻዮ ዶንግ ለረጅም ሰዓታት ስልኩ ላይ አቀርቅሮ በማሳለፉ የተነሳ በከፊል ፓራላይዝ ሆኗል።
ስልኩ ላይ ማኀበራዊ ሚዲያዎችን በመከታተል ሙሉ ጊዜውን በሚባል ደረጃ ላይ የሚያሳልፈው ወጣቱ ከጊዜ በኋላ በአንገቱ፣ በእጆቹ እና በእግሮቹ ላይ የመደንዘዝ ስሜት ይሰማው ጀመር።
ነገሮችም እየተባባሱ ሄደው አንድ ቀን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ እግሩ መንቀሳቀስ አቅቶት እንደነበር ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።
ዶክተሮችም በፍጥነት ወደ ቀዶ ጥገና ወስደውት በአከርካሪው ላይ ከፍተኛ የደም መርጋት መኖሩ አረጋገጡ።
ወጣቱ ያለማቋረጥ ስልኩ ላይ አቀርቅሮ ማሳለፉ በአከርካሪው ውስጥ ያለውን የደም ቧንቧ ተሰብሯል። ይህም ደም በውስጡ እንዲረጋ እና በከፊል ሽባ እንዲሆን አድርጓል ብለዋል ዶክተሮቹ።
እንደ ዕድል ሆኖ ግን፣ ሻዮ ዶንግ አሁን ላይ ቀስ በቀስ እንቅስቃሴን እያደረገ ሲሆን፤ ዶክተሮች ሙሉ በሙሉ እንደሚድን ያምናሉ።
አንገትን ለረጅም ጊዜ አቀርቅሮ ስልክ ላይ ማሳለፍ የደም ዝውውርን በመዝጋት ራስ ምታትን፣ ማዞርን፣ ድካምን እና መደንዘዝን እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።
ሁኔታዎች እየከፉ ሲሄዱ ደግሞ ወደ ስትሮክ ወይም ፓራላይዝ እስከመሆን ሊዳርግም ይችላል ይላሉ።
በሴራን ታደሰ
#EBC #EBCdotstream #paralyze #phone addiction