Search

ሀገር አቀፍ የኪነ-ጥበብ ውድድሩ ሕብረ ብሔራዊነትን ለማጉላት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል - የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር

ሰኞ ነሐሴ 26, 2017 42

ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የኪነ-ጥበብ ውድድር አሰባሳቢ ትርክት ግንባታ እና ህብረ ብሔራዊነትን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከነሐሴ 28 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ "ጥበባት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት" በሚል መሪ ሃሳብ የሚያካሂደውን ሁለተኛውን ሀገር አቀፍ የኪነ-ጥበብ ውድድር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በሰጡት መግለጫ ፤ በሁለተኛው ሀገር አቀፍ የኪነ-ጥበብ ውድድር 364 ባለተሰጥኦዎች ይሳተፋሉ ብለዋል።

ውድድሩ የሚከናወነው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ በሚመረቅበት ወቅት እንደመሆኑ የጥበብ ስራዎቹ ከግድቡ ጋር ተያያዥነት እንዳላቸው አመላክተዋል።

በብሔራዊ ቴአትር በሚካሄደው ውድድር የሙዚቃ፣ ውዝዋዜ፣ በባህላዊ አልባሳት የፋሽን ውድድር፣ የስዕልና መነባነብ ስራዎች እንደሚቀርቡም አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ‘ሆፕ ፎር ኢትዮጵያን ፒዩፕልስ’ ከተሰኘ የበጎ አድራጎት ማህበር ጋር አብሮ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምንት አድርጓል።

ስመመነቱ ኪነ-ጥበብን ለማጠናከር እና ለወጣት ባለተሰጥኦዎች ምቹ እድሎችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

በሴራን ታደሰ

#EBC #ebcdotstream #Arts