Search

የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ከቆሙ የተሻለ መሥራት እንደሚችሉ ማሳያ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ

ሰኞ ነሐሴ 26, 2017 44

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፅናታችን እና የአንድነታችን ማሳያ ነው ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ተናግረዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ የክልል፣ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች በተገኙበት በጋምቤላ ስታዲየም ሰሞኑን የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።

በወቅቱ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያዉያን የተባበረ ክንድ ለፍፃሜ መድረሱ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ከቆሙ የተሻለ መሥራት እንደሚችሉ ማሳያ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሯ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን ውስጣዊ እና ውጫዊ ፈተናዎችን በመሻገር ያሳኩት የአንድነታችን ማሳያ ነው ብለዋል።

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በራሳችን አቅም ለፍፃሜ መብቃቱ በመተባበር ጠንክሮ መሥራት ለድል ያበቃል የሚለውን መልዕክት በአግባቡ ያስተላለፈ መሆኑን አንስተዋል።

 

በቢታኒያ ሲሳይ

 #EBC #ebcdotstream #Ethiopia #GERD