ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ዘመን ከጂኦፖለቲካ ኩስመና ወደ ተሻለ ቁመና የተሻገረችበት ዘመን እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ኢትዮጵያውያን ስለ ዓባይ ለዘመናት ሲቆጩ እንደኖሩ እና ቁጭታቸውንም በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹ እንደነበር ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያወሱት፡፡
ቁጭታቸውን ከገለጹባቸው መካከልም የተለያዩ የዲፕሎማሲ ሙከራዎች እና ኪነ-ጥበባዊ መግለጫዎች እንደነበሩም ተናግረዋል፡፡
የዓባይ ጉዳይ በኪነጥበብ ከተገለጸባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ግጥም መሆኑን አስታውሰው፣ እነዚህ ሥራዎች የአሁኑ ትውልድ ስለ ዓባይ የደረጀ ሃሳብ እንዲይዝ አድርገዋል ብለዋል፡፡
ያለፉት ኢትዮጵያውያንም ሆኑ መሪዎች እንደ ሕዳሴ ግድብ ያለ ፕሮጀክት ለመገንባት ፍላጎት ቢኖራቸውም በተለያዩ ምክንያቶች ግን ዓባይ ላይ መሰራት እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡
እነዚህ ጥረቶች እና ቁጭቶች አሁን ያለው ትውልድ የደረጀ ሀሳብ እንዲይዝ ማስቻላቸውን ጠቁመው፣ የአሁኑ ትውልድም የነበረው የጂኦፖለቲካ ኩስመና እንደማይመጥነው ተረድቶ ወደ ተሻለ ቁመና ለመሸጋገር በቁርጠኝነት ወደ ሥራ የገባበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በለሚ ታደሰ
#PMOEthiopia #AbiyAhmed #EBC #ebcdotstream #GERD #naturalgift