ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የኩስመና ታሪክ ማብቂያ" በሚል ርዕስ ባደረጉት የጉባ ላይ ወግ፤ ከግድቡ በፊት የነበረችው ኢትዮጵያ እና ከግድቡ በኋላ የምትኖረው ኢትዮጵያ የተለያዩ ናቸው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የጂኦፖለቲካ ቁመና መሻሻሉን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለብዙ ሺሕ አመታት የኢትዮጵያውያን ጥያቄ የሆነው የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቁ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ በጂኦፖለቲካው ያላትን ተሰሚነት አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የሕዳሴው ግድብ ለኢትዮትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ታላቅ ሥራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ብዙዎቹ ችግሮቻችን የቅርብ ጊዜያት ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዓባይ ግን የብዙ ሺሕ ዘመን ጥያቄ ነው ብለዋል፡፡
ታድያ ይህን ችግር እና ጥያቄ የፈታ ትውልድ ለሌሎች ችግሮች የሚንበረከክ አይሆንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሚቀጥሉት ዓመታት ኢትዮጵያ የሕዳሴ አይነት በርካታ ፕሮጀክቶችን ጀምራ ታጠናቅቃለች ብለዋል፡፡
የሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ በርካታ አንድምታዎችን የሚያመጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የመጀመሪያው ግድቡ የጎንዩሽ ጉዳት ያመጣብናል ብለው ለሚያስቡት አካላት መልስ የሚሰጥና ግድቡ ተጠናቆ ያመጣው አንዳችም ተጽእኖ እንደሌለ የሚያረጋግጥ ሲሉ ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም ከተለያዩ አካላት ተልዕኮ ወስደው ሲሰሩ ለነበሩ አካላት መልስ የሚሰጥ እና የኢትዮጵያውያን አንድነት ምን ያህል እንደሆነ ያሳየንበት ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#PMOEthiopia #AbiyAhmed #EBC #ebcdotstream #GERD