የሕዳሴ ግድብ ላይ የተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ በኢትዮጵያ አንደኛው በአፍሪካ ደግሞ ከታላላቆቹ ሐይቆች አንዱ በመሆኑ ንጋት በሚል መሰየሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የኩስመና ታሪክ ማብቂያ" በሚል ርዕስ ባደረጉት የጉባ ላይ ወግ፤ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች ቢሆንም የተሰጠንን አውቀን መጠቀም ተስኖን የድህነት ምሳሌ የሆንበት የታሪክ ገፅ እንደሚያስቆጭ ገልጸዋል።
ለሕዳሴ ግድብ በርካታ መስዕዋትነት የከፈሉለት ሰዎች አሉ፤ አቅማቸው የፈቀደውን ያዋጡም እንዲሁ ብዙ ናቸው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ይሕን ሁሉ ዘመን ዓባይን እያየነው ሀብቶቻችንን ይዞ ሲሄድ ነበር ይሔን ለመረዳት በርካታ ጊዜ ፈጅቶብናል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
ለዘመናት የጠለቀ እንቅልፍ ውስጥ ነበርን ከእንቅልፋችን የነቃንበት እና ያሉንን ሀብቶች የተረዳንበት ጌዜ ላይ ያገኘነው በመሆኑ ንጋት ብለን ሰይመነዋል ነው ያሉት።
ንጋት የቀኑን ውሎ ለመጀመር የመጀመሪያው ቅጽበት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያም ንጋቷን በሕዳሴ አይታለች፤ ከዚሕ በኋላም በርካታ ሕዳሴዎችን ለመስራት ተነስታለች ብለዋል፡፡
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#PMOEthiopia #AbiyAhmed #EBC #ebcdotstream #GERD