በሱዳን በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ መንደር ነዋሪዎች ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል።
የመሬት መንሸራተቱ የተከሰተው ለቀናት ከጣለው ከባድ ዝናብ በኋላ ሲሆን፤ ቢያንስ የ1ሺ ሰዎች ሕይወት ማለፉም ነው የተገለፀው።
የመሬት መንሸራተቱ የተከሰተው በምዕራብ ሱዳን ዳርፉር ክልል ማራህ ተራራ ላይ በምትገኘው ታራሲን መንደር ነው።
በአደጋው ምክንያት የታርሲን መንደር አብዛኛው አካባቢ መውደሙን እና ከመንደሯ ነዋሪዎችም አንድ ሰው ብቻ በሕይወት መትረፉን ቢቢሲ ዘግቧል።
#EBC #EBCdotstream #landslide #Sudan