Search

ደቡብ አፍሪካ በሱዳን አፋጣኝ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቀች

ማክሰኞ ነሐሴ 27, 2017 65

የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ በሱዳን እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመፍታት እና ሰብዓዊ እርዳታ ያለእንቅፋት እንዲደርስ ለማድረግ ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲመለሱ ጠይቋል።

ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ በሱዳን ጦር እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች መካከል ባለው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።

በተለይም 500 ቀናት ያህል በከበባ ውስጥ የምትገኘው የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ ኤል ፋሸር ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆኗ ተገልጿል። ባለፈው ነሐሴ ወር በከተማዋ በተፈፀመ ድብደባ 24 ሰዎች ሲሞቱ፣ 55 የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ለሱዳን ህዝብ፣ በተለይ ለሴቶችና ለህፃናት አጋርነቱን ገልጿል። ጦርነቱ በወታደራዊ መንገድ ሊፈታ እንደማይችል በመጠቆም፣ ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲመለሱ እና የሲቪል መንግሥት እንዲመሰረት ጥሪ አቅርቧል።

በሰለሞን ገዳ