Search

ሕዳሴ ግድብ የመንግሥትና ሕዝብ የተቀናጀ ርብርብ ውጤት ነው - አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ነሐሴ 27, 2017 164

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አይችሉም፣ አይገነቡትም ያሉንን ያሳፈርንበት፤ የለውጡ መንግሥትና የሕዝቡ የተቀናጀ ርብርብ ውጤት ነው ሲሉ የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋዊ በርሄ (/) ገለጹ። 

/ር አረጋዊ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በለውጡ መንግሥትና የኢትዮጵያ ሕዝብ ትብብር ለውጤት በቅቷል። 

ሕዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን በአገር ውስጥም በውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን የገንዘብና የጉልበት ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በሞራል ያደረጉት ድጋፍ የሚመሰገን ነው ሲሉም ተናግረዋል። 

ግድቡ የገጠር እና ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም ያለው አበርክቶ ትልቅ መሆኑን ጠቁመው፤ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማሳለጥም ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል። 

"ግድቡ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የማንገፋው ተራራ እንደሌለ ማሳያ ነው" ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ህዝቡ በሌሎች ልማቶች ላይም ተሳትፎውንጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል። 

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ያለ ብድርና ዕርዳታ በራስ አቅም ማጠናቀቅ መቻላችንም ግድቡን መገንባት አይችሉም ያሉንን ያሳፈርንበት ነው ሲሉም ገልጸዋል። 

ግድቡ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት የልማት እርሾ እየሆነ ነው ያሉት /ር አረጋዊ፤ ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኃይል ለማስተሳሰር የምታደርገውን ጉዞም የተቃና እንደሚያደርገው አክለዋል። 

#EBCdotstream #GERD #ሕዳሴግድብ #Hidase #RenaissanceDam