በአፍጋኒስታን በደረሰው ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺ 400 መሻገሩን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
የታሊባን አስተዳደር ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ እንደገለፁት፥ በርዕደ መሬቱ ቢያንስ 1 ሺ 411 ሰዎች ሲሞቱ፤ 3 ሺህ 124 ሰዎች ቆስለዋል። በተጨማሪም ከ5 ሺህ 400 በላይ ቤቶች ወድመዋል።
አሁንም በፍርስራሽ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎች ይኖራሉ የሚል ስጋት ስለመኖሩ በአደጋው ክልል ውስጥ የሚሠራው የአፍጋኒስታን ቀይ ጨረቃ ማህበር ገልጿል።
በአፍጋኒስታን የሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት አስተባባሪ በበኩላቸው የጉዳቱ መጠን ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።
ሰኞ እኩለ ሌሊት ገደማ የተከሰተው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 6 የተመዘገበ ሲሆን፤ ምስራቃዊ ኩናር እና ናንጋርሃር ግዛቶች በአደጋው መጠነ ሰፊ ጉዳት ያስተናገዱ ናቸው።
#EBC #EBCdotstream #Afghanistan #Earthquake #deathtoll