Search

ዳያስፖራው በሕዳሴው ግድብ ትርጉም ያለው ሚና ተጫውቷል፦ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት

ማክሰኞ ነሐሴ 27, 2017 152

ዳያስፖራው በሕዳሴ ግድብ አምባሳደር በመሆን ትርጉም ያለው ሚና መጫወቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ  ከኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ዳያስፖራው  ላለፉት 14 ዓመታት ሕዳሴው  በገንዘብም ሆነ በተለያዩ መንገድ ድጋፍ በማድረግ ለሀገሩ አለኝታ መሆኑን አስመስክሯል ብለዋል፡፡

በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ከተለያዩ  ሀገራት ማስፈራራቶች ይደርሱ እንደነበር አንስተው፤ ዳያስፖራው በአንድነት በመቆም ያደረገው ተጋድሎ የሚደነቅ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያን ድምጻቸውን በዓለም አቀፍ አደባባዮች በማሰማት ትልቅ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውንም ነው ያስታወሱት፡፡

ሕዳሴ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን  ያሰባሰበ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

 

በሜሮን ንብረት