በዓለማችን ላይ ቡና ላይ እሴት ጨምረው ቆልተው፣ ፈጭተው እና አሽገው ለዓለም ገበያ የሚያቀርቡት ቡና የማያበቅሉ ሀገራት አሉ ቢባል ነገሩ ያስገርማል።
እንዴት? ካሉ ከሌሎች አምራች ሀገራት ቡናን በማስገባት እና እሴት በመጨመር ነው መልሱ።
በዚህም መሰረት በጀርመን የተለያዩ ከተሞች ከ500 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የቡና ማቀነባበሪያ ድርጅቶች ይገኛሉ።
እነዚህ የቡና ማቀነባበሪያ ኩባንያዎች ከብራዚል፣ ቪዬትናም እና ከሌሎች ሀገራት ጥሬ ቡናን በማስመጣት እና በማቀነባበር መልሰው ወደ ውጪ ሀገራት ይልካሉ።
በዚህም በየዓመቱ በቢሊየን ዶላሮች የሚቆጠር ገቢ እያገኙም ነው።
ቡናን ቆልቶ በመፍጨት እና አሽጎ በብዛት ለገበያ በማቅረብ ከዓለም በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ከምትገኘው ጀርመን በመቀጠል ሁለተኛ እና ሶስተኛ የሆኑት ደግሞ ስዊዘርላንድ እና ጣልያን ናቸው።
እነዚህም ሀገራት በተመሳሳይ ቡናን ለማብቀል የሚያስችል የአየር ንብረት ባይኖራቸውም ጥሬ ቡና አምራች ከሆኑ አገራት ይልቅ የቡና ኢንዱስትሪዎች በብዛት ስላላቸው ትርፋማ ናቸው።
ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ እና ሌሎች ቡናን በስፋት ለሚያመርቱ ሀገራት አንድ መልዕክት ያስተላልፋል።
እሱም ቡናን ከማምረት ባለፈ እሴት ጨምሮ ለገበያ ማቅረብ አዋጭ ስለመሆኑ።
ቡናን በማቀነባበር እና በተለያየ የቡና ውጤቶች ላይ በማተኮር ተጨማሪ ገቢ ማግኘት እንደሚቻል የአውሮፓውያኑ ሀገራት ተሞክሮ በቂ ማስረጃም ነው።
በዋሲሁን ተስፋዬ
#EBC #ebcdotstream #coffee