Search

የሱፍ እርሻ ልማት በአፋር አሚባራ

ማክሰኞ ነሐሴ 27, 2017 54

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሐጂ አወል አርባ በአሚባራ ወረዳ እየለማ የሚገኝ የሱፍ እርሻን ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ ጉብኝታቸው ላይ እንደተናገሩት፤ ወደ ሀገር የሚገቡ የዘይት ምርቶች በሀገር ምርት ለመተካት በአፋር ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የሱፍ ምርት በሰፊው እየተሰራበት ይገኛል።

 

ኢትዮጵያ ለግብርና ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ለመሆኗም የአሚባራው ልማት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

በግብርናው ዘርፍ ኢንቨስትመንትን የማሳደግ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 

ርዕሰ መስተዳድሩ የጎበኙት በግል ባለሃብት እየለማ የሚገኝ 500 ሄክታር የሱፍ እርሻ ሲሆን በዚህም ለአካባቢው ማኀበረሰብ ከፍተኛ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አንስተዋል። 

በሁሴን መሀመድ

 

#EBC  #ebcdotstream  #Afar #Agriculture

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: