Search

የቻይና 80ኛ ዓመት የድል በዓል

ማክሰኞ ነሐሴ 27, 2017 51

ቻይና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቅ በኋላ 80ኛ ዓመት የድል በዓሏ ላይ ደርሳለች። 

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት እንዲሁም ከጦርነቱ ፍፃሜ በኋላ የቻይና ወዳጅ በመሆን ያሳለፉ  ሀገራት እና እንግዶች በተገኙበት የ80ኛ ዓመቱ በዓል ዋዜማም በተለያዩ መሰናዶዎች ተከብሯል።

የዝክረ በዓሉ ዋና ማጠንጠኛም ሰላም ነበር። 

በዝክረ በዓሉ ላይ የቻይና የረጅም ጊዜ ወዳጆች የሆኑ አምስት ግለሰቦች የተጋበዙ ሲሆን፤ ተጋባዥ እንግዶቹ ከ65-74 ዕድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። 

እነዚህ ሰዎች ከቻይና ጋር በወዳጅነት ለበርካታ ዓመታትን አሳልፈዋል።  እድሜያቸውን እውቀታቸውን እና ሕይወታቸውንም ጭምር የሰጡ በተለይ ከሰላም ጋር በተያያዘ ሲሰሩ እየቆዩ ሰዎች ናቸው።

በዋዜማው ዝክረ በዓል ላይ በርካታ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን፤ በተለይም የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት በማንሳት ጦርነት ምን ያህል አስከፊ እንደነበረ ተነስቷል። 

ነገ ስለሚከበረው የ80ኛ ዓመት የቻይና የድል በዓል በማንሳትም እንደዚህ አይነት የድል በዓላት ሲከበሩ ያለፈውን ታሪክ እያነሱ ቁርሾው ማስቀመጥ ሳይሆን አሁን ላይ ያለውን እድገት፣ ሰላም፣ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያለውን ወዳጅነት የሚከበርበት መሆኑም ተመላክቷል።

ነገ የ80ኛ ዓመት የድል በዓሉ በቻይና ቤጂንግ ሚሊኒየም ሞነመንት ፖርክ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ከፍተኛ የቻይና የመንግስት ባለስልጣናት፣ጥሪ የተደረገላቸው የዓለም መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የተለያዩ ሃገራት ጋዜጠኞች እና እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ተብሎ ይጠበቃል። 

በተለይም ቻይና በዓለም መድረክ የምትደነቅበት ወታደራዊ ትዕይንት እጅግ ተጠባቂ ነው። በዓሉ በበርካታ ሃገራትም በተለያዩ ቋንቋዎች የቀጥታ ስርጭት ያገኛል ተብሏል።

 

ነፃነት ክንፈ

#EBC  #ebcdotstream  #china