Search

በአሶሳ ለኮሪደር ልማት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና ተሰጠ

ማክሰኞ ነሐሴ 27, 2017 45

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ለተከናወነው የኮሪደር ልማት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ።

በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፤ የኮሪደር ልማት ሥራው ሕዝብ ሰላሙን በመጠበቅ ልማቱንም ማከናወን እንደሚችል ያረጋገጠ ነው ብለዋል። 

ክልሉ ካለው የተፈጥሮ ሃብት አንፃር የመልማት አቅሙን ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልፀው፤በአሶሳ የተከናወነው የልማት ሥራ በቀጣይ በጀት ዓመት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በቀጠይ የአሶሳ፣ የግልገል በለስ ከተማ፣ የባምባሲ ከተማ እና የካማሺ ከተማ የኮሪደር ልማት እንደሚሰራ  ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል።

በከተማዋ የተከናወነው የ9.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኮሪደር ልማት የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራዎች፣ የሳይክል እና የእግረኛ መንገዶችን እንዲሁም የልጆች መጫወቻ ቦታዎችን ያካተተ ነው።

ለኮሪደር ልማቱ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሀብቶች፣ተቋማት እና ግለሰቦች በቀጣይም የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

 

በነስረዲን ሀሚድ

#EBC  #ebcdotstream  #Corridor #development

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: