Search

እያሴሩብን ነው:- ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ረቡዕ ነሐሴ 28, 2017 87

ፕሬዝዳንት  ዶናልድ ትራምፕ ቻይና፣ ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ላይ እያሴሩ ነው ሲሉ ከሰዋል።  

ትራምፕ ይህን ያሉት ቻይና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጃፓንን ድል ማድረጓን ለማክበር ቤጂንግ ውስጥ ያዘጋጀችውን ወታደራዊ ሰልፍ ተከትሎ ነው።

ትራምፕ “ብዙ አሜሪካውያን በቻይና የድልና የክብር ጥረት ውስጥ ህይወታቸውን አጥተዋል። ለጀግንነታቸውና ለፅንዓታቸው በትክክል እንደሚከበሩና እንደሚታወሱ ተስፋ አደርጋለሁ!” በማለት ጽፈዋል።

ለቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግ መልካም ምኞታቸውን ከገለጹ በኋላ “ከአሜሪካ ጋር ሴራ እየጠነሰሱ ያሉትን ቭላድሚር ፑቲን እና ኪም ጆንግ-ኡንን የእኔን ሞቅ ያለ ሰላምታ እንዲያደርሱልኝ” ሲሉ አክለዋል።

ትራምፕ በበዓሉ ላይ ያልተገኙ ሲሆን ከቻይናና ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በንግድ ጦርነት፣ በቅጣትና በዩክሬን ግጭት ሳቢያ ውጥረት እንደነገሰበት ቀጥሏል።

ቻይናና ሩሲያ አሜሪካ ዓለም አቀፍ ደረጃ  ፍላጎቷን በሌሎች ላይ ለመጫን እየሞከረች ነው ሲሉ ይከስሳሉ።

በሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ላይ፣ ዢ “የቀዝቃዛው ጦርነት አስተሳሰብ” እንዲያከትም እና “ፍትሃዊ” ዓለም አቀፍ ግንኙነት ለመፍጠር አብሮ ለመስራት ጥሪያቸውን አድሰዋል። 

በሰለሞን ገዳ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: