የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡንን ጨምሮ የ26 ሀገራት መሪዎች የታደሙበት የቻይና ወታደራዊ ትርዒት በቤጂንግ ተካሂዷል፡፡
በቲያናንመን አደባባይ የተካሄደው የቻይና ወታደራዊ ትርዒት በዓል ቻይና ከጃፓን ጋር ያደረገችው ጦርነት እና 2ኛው የዓለም ጦርነት የተጠናቀቀብትን 80ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክቶ ነው የተከናወነው፡፡
ቻይና "የድል ቀን" ብላ በሰየመችው በዚህ ወታደራዊ ትርዒት ዓለም አይቷቸው የማያውቃቸውን እጅግ የተራቀቁ ወታደራዊ ትጥቆቿን ለዕይታ ማቅረቧ ተነግሯል፡፡
በወታደራዊ ትርዒቱ ላይ ከቻይና የመከላከያ ጦር፣ ከባህር ኃይል እና አየር ኃይል የተውጣጡ ከ10 ሺህ በላይ ወታደሮች መሳተፋቸው ተጠቅሷል፡፡
በትርዒቱ ላይ የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎች፤ የሌዘር (ጨረር) የአየር መቃዎሚያዎች፣ የኑክሌር ማሳሪያዎች፣ ባለስቲክ ሚሳኤሎች እንዲሁም የተለያዩ የድሮን ማሳሪያዎች ለእይታ መቅረባቸው ተገልጿል፡፡
በወታደራዊ ትርዒቱ ላይ ፑቲን እና ኪምን ጨምሮ የ26 ሀገራት መሪዎች መታደማቸውን የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡
#ebc #ebcdotstream #china #militaryparade