የአፍሪካ ኅብረት፣ አሜሪካ ስደተኞችን ወደ ሦስተኛ ሀገሮች ለመላክ ከምትፈጽማቸው ስምምነቶች ጋር በተያያዘ አፍሪካ ለስደተኞች "መጣያ ስፍራ" ልትሆን ትችላለች በሚል ስጋቱን ገልጿል።
ኅብረቱ ስደተኞችን ምንም ዓይነት ግንኙነት ወደሌላቸው የአፍሪካ ሀገሮች መላክ ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሊያጋልጣቸው እንደሚችል ያሳስባል። ይህ ኃላፊነትን ወደ ሌላ አካል ማዞር ነው ሲልም ይከራከራል።
እንደ ናይጄሪያ ያሉ ሀገሮች አሜሪካ የአፍሪካ አገሮችን ቪዛን በመገደብ እና ቀረጥ በመጨመር ስደተኞችን እንዲቀበሉ እንደምትገፋፋቸው ይከሳሉ። ናይጄሪያ ከአሜሪካ እስር ቤቶች የተለቀቁ ሰዎችን ጨምሮ ማንኛውንም ስደተኛ እንደማትቀበል በግልጽ አስታውቃለች።
እስካሁን አራት የአፍሪካ አገሮች ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢስዋቲኒ አሜሪካ ስደተኞችን ወደ ግዛታቸው እንድትልክ ስምምነት መፈረማቸው ይታወቃል።
ይህ ጉዳይ መጀመሪያ ላይ በተደበቀ መልኩ ቢጀመርም፣ አሁን ግን ሰፊ ትችት እየገጠመው ነው።
በሰለሞን ገዳ