Search

ከብዙ መከራ በኋላ ህዳሴ ለምርቃት በመብቃቱ ልዩ ደስታ ፈጥሮብኛል - ኡስታዝ ጀማል በሽርከብዙ መከራ በኋላ ህዳሴ ለምርቃት በመብቃቱ ልዩ ደስታ ፈጥሮብኛል - ኡስታዝ ጀማል በሽር

ረቡዕ ነሐሴ 28, 2017 74

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከብዙ መከራ በኋላ ለምርቃት በመብቃቱ ልዩ ደስታ እንደፈጠረባቸው የኪንግስ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ ሥራ አስኪያጅ ኡስታዝ ጀማል በሽር ገለፁ፡፡

በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደቱን በማጠልሸት ቅቡልነት ለማግኘት ግብጾች የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ኡስታዝ ጀማል ገልፀዋል፡፡

ግብጾች ከ200 በላይ የቴሌቭዥን ጣቢያዎችና ዲጂታል ሚዲያዎችን ተጠቅመው ስለ ኢትዮጵያና ህዳሴው ግድብ ግንባታ የተሳሳቱ ዜናዎችን፣ ፕሮግራሞችንና መረጀዎችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደሚያሰራጩ ተናግረዋል፡፡

ግብጾች ያላቸውን የቴሌቭዥንና የዲጂታል ሚዲያ አማራጮችን ተጠቅመው የህዳሴው ግድብ፤ የግብጽን የውኃ ድርሻ በመቀማት ብሄራዊ የደህንነት ስጋት እንደሚፈጥር አድርገው ሀሰተኛ መረጃ ያሰራጫሉ ብለዋል ኡስታዝ ጀማል፡፡

በዲጂታል ሚዲያ ንቅናቄው የዓረቡ ዓለም እውነታውን እንዲረዳ፣ የህዳሴው ግድብ የሚይዘው ውኃ የታችው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት እንደማያስከትል ትክክለኛ መረጃ በመስጠት በርካታ የዓረብ ሀገራት ግለሰቦች ለህዳሴው ግድብ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉን ኡስታዝ ጀማል ተናግረዋል፡፡ 

ግብጾች ከመጠን በላይ የተከማቸ ውኃ አላቸው የሚሉት ኡስታዝ ጀማል፤ ቱሽካ በረሃ ላይ የሚለቁት ውኃ መጠን ከ80 እስከ 120 ቢሊዮን ኪዩብክ ሜትር እንደሚደርስ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል፡፡

መሀመድ አል አሩስን ጨምሮ ሌሎች የዲጂታል ሰራዊቶች የሀገራቸውንና የህዳሴውን ግድብ የተመለከቱ የተሳሳቱና አሉታዊ ትርክቶችን በማረምና ምላሽ በመስጠት ሂደት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ያነሱት ኡስታዝ ጀማል፤ ይህ አልፎ ህዳሴ ለምርቃት በመብቃቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኡስታዝ ጀማል በሽር ስለ ህዳሴ ግድብ በሚዲያ ከሚሞግቱት ስራ ጎን ለጎን ቦንድ በመግዛትና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር ቦንድ እንዲገዙ በማድረግ አርዓያ የሆነ ተግባር ፈጽመዋል፡፡

በመሀመድ ፊጣሞ

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #GERD