ቻይና 2ኛው የዓለም ጦርነት ያበቀበትን እና በጃፓን ላይ ያገኘችውን ድል 80ኛ ዓመት በዓል ለማክበር ታላቅ ወታደራዊ ትርዒት በቤጂንግ አሳይታለች።
የቻይና ዘመናዊ ወታደራዊ አቅም ማሳያ በሆነው በዚህ ወታደራዊ ትርዒት ላይ ከ10 ሺህ በላይ ወታደሮች የተሳተፉ ሲሆን፤ የቻይናን የቅርብ ጊዜ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች የሚያሳዩ በሰከንድ 3 ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችሉ አገር አቋራጭ ሚሳኤሎች በቤጂንግ ጎዳና በሰልፍ ቆመው ታይተዋል።
እንዲሁም ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችና ከ160 በላይ የሚሆኑ የጦር ጀቶች በትርዒቱ የተካፈሉ ሲሆን፤ ዘመናዊ ታንኮች፣ ለስለላና ለወታደራዊ ግዳጆች የሚያገለግሉ ሰው አልባ የውሃ ውስጥ ድሮኖችና በጨረር የሚሰሩ ፀረ ድሮን መሳሪያዎች ለእይታ ቀርበዋል።
ዛሬ በተካሄደው በቻይና ታሪክ ታላቅ በተባለውና ሀገሪቱ አሉኝ የምትላቸውን እጅግ ዘመናዊ ወታደራዊ መሳሪያዎች ባሳየችበት በዚህ ወታደራዊ ትርዒት ማብቂያ ላይ ሰማንያ ሺህ ነጭ እርግቦችና ሰማንያ ሺህ ፊኛዎች ተለቀው በሰማይ ላይ ሲበሩና ሲንሳፈፉ የታዩ ሲሆን፤ ይህም ቻይና ለሰላም ያላትን ፍላጎት ያሳየ ነው ተብሏል።
በዋሲሁን ተስፋዬ
#China #VDay #Beijing #TiananmenSquare #militaryparade