በኢትዮጵያ ከሚለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ይበዛሉ፤ በመለያየት እና በፀብ የሚያተርፍ የለም፣ ኪሳራ እንጂ ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱልከሪም ሐጂ በድረዲን ገልጸዋል።
1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጂድ እየተከበረ ይገኛል፤ በዚህ ወቅት ሼህ አብዱልከሪም ሐጂ በድረዲን በዓሉ የአንድነት እና የሰላም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የታላቁ ነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የልደት በዓልን የምናከብረው ለሀገር ሰላም፣ እድገት እና አንድነት ትልቅ ትርጉም ያለው እና የላቀ በመሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
“ለሀገር አንድነት ሲባል የትጥቅ ትግል ያነገባችሁ በጨካ የምትገኙ ወንድሞች፣ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብላችሁ ሰላማዊ የትግል አማራጭ በመጠቀም ወደ ቤታችሁ እንድትመለሱ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በዓሉ ለነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) ያለንን ፍቅር የምንገልፅበት ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዓሉን ለተቸገሩ በማካፈል ማክበር አለበት ብለዋል።
በመሐመድ ፊጣሞ
#etv #EBC #ebcdotstream #መውሊድ #mewlid