Search

የባዕዳን ተልዕኮ ያላስቆመው ሕዳሴ ግድብ

ሓሙስ ነሐሴ 29, 2017 62

የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራትን ተልዕኮ የወሰዱ አካላት ግድቡ አካባቢ ቦንብ በመቅበር ጭምር አደጋ ለማድረስ መሞከራቸውን ያስታውሳሉ የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ።
ይሁንና ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ፈንጂውን በማምከን ሕይወቱን ሰውቶ የግድቡን ግንባታ እዚህ እንዲደርስ አድርጓል ሲሉ ይገልጻሉ።
ከዚህም ባለፈ የሕዳሴ ግድብ ሥራ ከተጀመረ በኃላ ልምድ የሌለው ኮንትራክተር ደካማ አፈጻጸም በማሳየቱ ፕሮጀክቱን አደጋ ላይ ጥሎት እንደነበር ያስታውሳሉ።
በፈተና የተሞላው እና ጥራቱን ያልጠበቀው ፕሮጀክቱ ለዓመታት መጓተቱን አንስተዋል።
የለውጡ መንግሥት ከመጣ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሥራውን መገምገማቸውን አስታውሰው፤ የኮንትራት ይዘቱን ቀይረው ሕዳሴ ግድብን ነፍስ ዘርተውበታል ይላሉ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለው ለድል ያበቁት ፕሮጀክት መሆኑንም ይገልጻሉ።
ሕዳሴ ግድብ እንደ ዳግማዊ ዐድዋ የሚታይ ነው ይላሉ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ።
 
በቢታኒያ ሲሳይ