የሕዳሴ ግድብ የዲፕሎማሲ ጉዞ ኢትዮጵያ እንዴት መብቷን ማስከበር እንዳለባት፣ እንዴት መደራደር እንዳለበት፣ እንዴት መቅረብ እንዳለበት አሳይታ እና ተምራበት እንደወጣች የሕዳሴ ግድብ የድርድር ቴክኒክ ኮሚቴ አባል በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ገለፁ።
ግብፅ ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ ከሳሽ ሆና ትቀርብ የነበረ ቢሆንም ፤ ኢትዮጵያ የሚመጡባትን የዲፕሎማሲ ጫናዎች በእርጋታ፣ በጥበብ፣ በማስተዋል እና ሀገርን በማስቀደም መወጣቷን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ስትገነባ በግብፅ ላይ ጉዳት ሳያደርስ በፍትሃዊ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ተንተርሶ መሠራቱን ተናግረዋል።
የድርድር ኮሚቴው በተለያዩ ጊዜያት የሚነሱ ሀሳቦችን በጥልቀት በማጤን እና ፍትሃዊ የአጠቃቀም መርህን በመከተል ድርድሩን በድል እንደተወጣ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ለሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም እንዲረጋገጥ በመሞገት ሉዓላዊነቷን ማስከበሯንም አንስተዋል።
በቢታንያ ሲሳይ
#EBCdotstream #ETV #Ethiopia #GERD #RenaissanceDam #ሕዳሴግድብ