Search

ኪን-ኢትዮጵያ የጥበብና ባህል ጉዞ በሩሲያ ሊካሄድ ነው

ዓርብ ነሐሴ 30, 2017 63

ከዚህ ቀደም በቻይና የተደረገው ይህ የጥበብና የባህል ጉዞ በሩሲያ ሁለት ከተሞች ይካሄዳል ተባለ።
በሩሲያ የሚደረገውን ሁለተኛው ዙር ኪን-ኢትዮጵያ የጥበብና ባህል ጉዞን በተመለከተ፤ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።
በሩሲያ በሚካሄደው ኪን-ኢትዮጵያ የጥበብና ባህል ጉዞ 65 በላይ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት ሲሆን፤ በርካታ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ትዕይንቶች የሚቀርቡበትም ይሆናል ተብሏል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፥  ሁለተኛው የኪን ኢትዮጵያ ጉዞ ከጳጉሜ 4 ቀን 2017 እስከ መስከረም 5 ቀን 2018 . በሩሲያ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
በሴንት ፒተርስበርግና ሞስኮ በሚካሄደው የጥበብ ትዕይንት የተለያዩ ኹነቶች እንደሚካሄዱም ነው የገለጹት
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በበኩላቸው፤ ኪን ኢትዮጵያ ጉዞ ኢትዮጵያን ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ እንደሆነ አንስተዋል።
በአባዲ ወይናይ