Search

አንድነት ኃይል ነው የሚለውን በተግባር ያሳየው የሕዳሴ ግድብ

ዓርብ ነሐሴ 30, 2017 15

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተለያዩ ፈተናዎችን አልፎ ለምርቃት መድረሱ እንደሕዝብ ከሚለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድነታችን ኃይል እንዳለው በቂ ማሳያ ነው ይላሉ በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ዜጎች።
ሕዳሴ ሕብረት ኃይል መሆኑን በማሳየት ለቀሪ የልማት ሥራዎች በቁጭት የሚያነሳሳ ፕሮጀክት ነው ሲሉም ሃሳባቸውን ለኢቢሲ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ስኬቱ እንደዐድዋ ድል የሚታይ ቢሆንም ኢትዮጵያውያን በዚህ ብቻ ሳይቆሙ ሌላም የልማት ሥራዎች መጠቀል እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያውያን በአንድነት የሰሩት ታሪክ መላውን ዜጋ ከዳር እስከ ዳር በቀና ስሜት ያሰባሰበ መሆኑንም አንስተዋል።
የሕዳሴ ግድብ በብሔር እና በዘር ሳንከፋፈል አንድ አድርጎ ያስተሳሰረን ሌላኛው የልማት አውድ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
በራሳችን አቅም እና ገንዘብ ያሳካነው ይህ ትልቅ ድል ለሌሎች አፍሪካ ሀገራትም ይቻላልን ያስተማርንበት በመሆኑ የልማት ጉዟችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ሲሉም ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
ነዋሪዎቹ ለግድቡ ያልተቋረጠ ድጋፍ እንዳደረጉ ገልጸው፤ በግድቡ ግንባታ የታየው ሕብረት በሌሎች ፕሮጀክቶች ላይም መደገም እንዳለበትም ነው ያነሱት፡፡
 
በሜሮን ንብረት